Song Lyrics

ቅዱስ እግዚአብሔር

Kalkidan (Lili) Tilahun
Legziabher Kelal New
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ንጹህ ፍፁም ነውር የሌለህ (2x) አንተ ነውር የለህም አንተ እድፈት የለህም አንተ ጉድለት የለህም አንተ እንከን የለህም (2x) አንተ ራስህ እውነት ነህ ምንም ውሸት የለብህ ኦ የለብህ (2x) ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ንጹህ ፍፁም ነውር የሌለህ (2x) አንተ ነውር የለህም አንተ እድፈት የለህም አንተ ጉድለት የለህም አንተ እንከን የለህም (2x) ታድያ እኔ ተስፋዬ እግዚአብሔር አይደለም ዎይ (2x) አሁንስ ተስፋዬ ማነው እግዚአብሔር አይደለም ዎይ (2x) ጠቢብ በጥበቡ አይመካ ኃያልም በኃይሉ አይመካ ፍርድና ጽድቅን በምድር ላይ የሚያደርግ እርሱ መሆኑን በማወቁ ብቻ በዚያ ይመካ (2x) አውቄያለሁና ጠንቅቄ ያላንተ ተስፋ እንደሌለኝ ያላንተ ተስፋ እንደሌለኝ (2x) አንተን የታመነ ሰው ሌላ ሌላ ሳይደምር/ሳይጨምር የተረጋገጠ ነው ፍጻሜው እንደሚያምር (2x) ታድያ እኔ ተስፋዬ እግዚአብሔር አይደለም ዎይ (2x) አሁንስ ተስፋዬ ማነው እግዚአብሔር አይደለም ዎይ (2x) አዋቂው በዕውቀቱ አይመካ ጻድቁም በጽድቁ አይመካ ፀላይም በፀሎቱ አይመካ ጿሚዉም በመጾሙ አይመካ ፍርድና ጽድቅን በምድር ላይ የሚያደርግ እርሱ መሆኑን በማወቁ ብቻ በእርሱ ይመካ (2x) ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ንጹህ ፍፁም ነውር የሌለህ (2x) አንተ ነውር የለህም አንተ እድፈት የለህም አንተ ጉድለት የለህም አንተ እንከን የለህም (2x) አንተ ራስህ እውነት ነህ ምንም ውሸት የለብህ ኦ የለብህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection