አዝ፦ ጌታ እኮ ነው የሚባርከኝ ጌታ እኮ ነው የሚያድርግልኝ ጌታ እኮ ነው የሚደርስልኝ ጌታ እኮ ነው የሚመጣልኝ እስኪቀደድ እስኪያፈስ መረቤ የባረከኝ ተገኝቶ አጠገቤ ባለቀለት ባበቃው ነገር ላይ አደረገኝ ትንሳኤውን እንዳይ ባከተመው በሞተው ነገር ላይ አደረገኝ ትንሳኤውን እንዳይ አዝ፦ ጌታ እኮ ነው የሚባርከኝ ጌታ እኮ ነው የሚያድርግልኝ ጌታ እኮ ነው የሚደርስልኝ ጌታ እኮ ነው የሚመጣልኝ ጌታ እኮ ነው አታዩትም ወይ የባረከኝ ከአቅሜ በላይ ልጐትተው አልቻልኩትምና ጓደኞቼ እርዱኝ ተገኙና ልሸከመው አልቻልኩትምና ወዳጆቼ እርዱኝ ተገኙና አዝ፦ ጌታ እኮ ነው የሚያሳካልኝ ጌታ እኮ ነው የሚያቃናልኝ ጌታ እኮ ነው ያትረፈረፈኝ ጌታ እኮ ነው ያረሰረሰኝ እዛጋ ጣዪው መረቡን ሚለኝ አሄ ብዬ መረቤን ጣልኩኝ በበረከቱ አስደነገጠኝ ይሄን ሁሉ መቼ ጠበኩኝ በበረከቱ አስደነገጠኝ ይሄን ሁሉ መቼ ጠበኩኝ አዝ፦ ጌታ እኮ ነው ክብር የሰጠኝ ጌታ እኮ ነው ሞገስ የሰጠኝ ጌታ እኮ ነው ውበት የሆነኝ ጌታ እኮ ነው . (1) . በረከቱን መቼ ላከልኝ እርሱ ራሱ ነው መጥቶ የሰጠኝ በሰው መጠቀም አላስፈለገውም ኢየሱስ ነው ቤቴ የገባው በሰው መጠቀም አላስፈለገውም ጌታዬ ነው ቤቴ የገባው አዝ፦ ጌታ እኮ ነው የሚያሸልለኝ ጌታ እኮ ነው የሚያዘንጠኝ ጌታ እኮ ነው ያንቀባረረኝ ላመስግነው ለቀቅ አድርጉኝ ጌታ እኮ ነው የሚያሸልለኝ ጌታዬ ነው የሚያዘንጠኝ ጌታዬ ነው ሕይወት የሰጠኝ ላመስግነው ለቀቅ አድርጉኝ