Song Lyrics

ትልቅ ነህ

Kalkidan (Lili) Tilahun
Beyet Hager New Egziabher
ትልቅ ነህ የእኔ አእምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ (4x) ኦ ትልቅ ነህ አንተ ትልቅ (3x) ኦ ትልቅ ነህ አንተ ትልቅ (3x) እግዚአብሔር ትልቅ ነው አምላኬ ትልቅ ነው (2x) ትልቅነትህን ያላየ ማነው (3x) ትልቅነትህን ያልሰማ ማነው (3x) እኔስ አይቻለሁ ትልቅነትህን ከሁኔታ በላይ አንተ መብለጥህን እኔ እንኳን አይቻለሁ ትልቅነትህን ከነገሮች በላይ አንተ መብለጥህን እኔ አይቻለሁ ትልቅነትህን ከሁኔታዎች አንተ መብለጥህን አንተ እኮ እጅግ ትልቅ ነህ (2x) አምላኬ እጅግ ትልቅ ነህ (2x) በሠማዩ ስፍራ በክብር ላለኸው ምሥጋናዬ ይኸው ምሥጋናዬ ይኸው በሠማዩ ስፍራ በክብር ላለኸው አምልኮዬ ይኸው አምልኮዬ ይኸው አይመረመርም ከፍ ማለቱ የእርሱ ልቀቱ ጌታዬ አይመረመርም ተወዳዳሪ አቻ ማጣቱ ጌታዬ አይመረመርም ውበት ቁንጅና ድምቀት ማማሩ ጌታይ አይመረመርም ግርማ ሞገሱ አስፈሪነቱ ጌታዬ ሃ ሃ ሃሌሉያ (4x) አይመረመርም የርህራሄው የምህረቱ ብዛቱ አይመረመርም ቸርነቱ ይቅር ማለቱ ጌታዬ አይመረመርም ፍቅሩ ጥልቀቱ ወርዱ ስፋቱ አይመረመርም ሰውን መውደዱ አዳኝነቱ ጌታዬ ሃ ሃ ሃሌሉያ (4x) ትልቅ ነህ የእኔ አእምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ (4x) ኦ ትልቅ ነህ አንተ ትልቅ (3x) ኦ ትልቅ ነህ አንተ ትልቅ (3x) እግዚአብሔር ትልቅ ነው አምላኬ ትልቅ ነው (2x) ትልቅነትህን ያላየ አለ ወይ? (3x) ትልቅነትህን ያልሰማ አለ ወይ? (3x) እኔኮ አይቻለሁ ትልቅነትህን ከሁኔታ በላይ አንተ መብለጥህን እኔ አይቻለሁ ትልቅነትህን ከሁኔታዎች አንተ መብለጥህን አንተ እኮ እጅግ ትልቅ ነህ (2x) አምላኬ እጅግ ትልቅ ነህ (2x) የዘለዓለም አምላክ የምድር ፈጣሪ በዘለዓለም ዙፋን ላይ ለዘለዓለም ነዋሪ የዘለዓለም አምላክ ነፍሴ ታከብርሃለች (2x) የነገሥታት ንጉሥ ነፍሴ ታከብርሃለች (2x) የዘለዓለም አምላክ ነፍሴ ታከብርሃለች (2x) ነፍሴ ታከብርሃለች (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection