Song Lyrics

አመልካለሁ

አመልካለሁ እጆቼን አንስቼ ጥያቄዬን ሁሉ እረስቼ ዓላማዬ አንተ ብቻ ነህ ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ ዓላማዬ አንተ ብቻ ነህ ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ (2x) ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (4x) ሁልጊዜ ሥምህን እጠራለሁ እጠራለሁ ኢየሱስ ኢየሱስ እልሃለሁ እልሃለሁ (2x) እልሃለሁ እልሃለሁ እልሃለሁ እልሃለሁ ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (4x) እንደ ማር ጣፈጠኝ ሥምህ አፌ ላይ ከሥምህ የሚበልጥ ሥም ይገኛል ወይ (2x) ሥሞች ተሰብስበው ለሥምህ ሰገዱ ከሥማቸው ይልቅ ሥምህን ወደዱ (2x) ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (4x) ምስጢሩ ምንድን ነው ምስጢሩ ይኼ ነው ሥሙን ያስወደደው በሃሪው እኮ ነው (2x) ሥሙና ሕይወቱ አንድ ላይ ይሄዳል እንደ ኢየሱስ ያለ ከወዴት ይገኛል (2x) ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (4x) እሺ ባይነትህ ታዛዥነትህ ክብርህን ለመጣል ክብር መጣልህ (2x) ዝቅ ዝቅ ማለትህ ከፍ ከፍ አድርጐሃል ከሥሞች የሚበልጥ ሥምን አሰጥቶሃል (2x) ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (4x) አመልካለሁ እጆቼን አንስቼ ጥያቄዬን ሁሉ እረስቼ ዓላማዬ አንተ ብቻ ነህ ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ ዓላማዬ አንተ ብቻ ነህ ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (4x) ምነው ነፍሴ እንደ ውኃ በሆንልኝ አምላኬ ፊት እንደ ጅረት ቢፈስልኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection