የነበረ ያለ የሚኖር እግዚአብሔር ብቻ ነው ፍጥረት ሁሉ በመደንቅ የሚከታተለው (2x) የነበረው ሁሉ በነበር አለቀ የድሮ ታሪክ ነው እጅጉን የራቀ ድሮም ዛሬም ነገም ነበረ ኃያል ሆኖ በዘመናት መሃል እግዚአብሔር ብቻ ነው የነበረ ያለ የሚኖር እግዚአብሔር ብቻ ነው ፍጥረት ሁሉ በመደንቅ የሚከታተለው (2x) አዝ፦ አንተ አትለዋወጥም አሃ አንተ ኃይልህ አይቀንስም አዎ አንተ ዘመንህ አያልቅም አሃ አንተ ጉልበትህ አይዝልም አሃ (2x) አትለዋወጥም አሃሃ (፲6x) እኔ እኮ የሚገርመኝ ሁልጊዜ ያው መሆንህ ነው (2x) እኔ እኮ የሚደንቀኝ ሁልጊዜ ያው መሆንህ ነው (8x) አዝ፦ አንተ አትለዋወጥም አሃ አንተ ኃይልህ አይቀንስም አዎ አንተ ዘመንህ አያልቅም አሃ አንተ ጉልበትህ አይዝልም አሃ (2x) አትለዋወጥም አሃሃ (፲6x) አይተናል አዎ ኃያላን ሲያልፉ አይተናል አዎ ብርቱዎች ሲደክሙ አይተናል አዎ ቁንጅና ሲያልፍ አይተናል አዎ ውበት ሲረግፍ (2x) አዝ፦ አንተ አትለዋወጥም አሃ አንተ ኃይልህ አይቀንስም አዎ አንተ ዘመንህ አያልቅም አሃ አንተ ጉልበትህ አይዝልም አሃ (2x) አትለዋወጥም አሃሃ (፲6x) እነ ኃያላን እነ አለቆች እነ ነገሥታት እነ አልሞት ባዮች አንድ በአንድ ሁሉም ሁሉም አለፉ እያየናቸው ከምድር ላይ ጠፉ (2x) አንተ ግን አትለዋወጥም አሃ አምላኬ አትለዋወጥም አሃ አምላክህ አይለዋወጥም አሃ አምላክሽ አይለዋወጥም አሃ እርሱ እኮ አይለዋወጥም አሃ አምላኬ አይለዋወጥም አሃ አምላክህ አይለዋወጥም አሃ አምላክሽ አይለዋወጥም አሃ አትለዋወጥም አሃሃ (፲6x) ትልቅ ነህ ሰፊ ነህ ጥልቅ ነህ ረቂቅ (2x) በዓይኔ በብረቱ አይቻለሁ አሃ ትልቅነትህን አይቻለሁ አሃ የማይሆነው ሲሆን አይቻለሁ አሃ ያለቀ ሲጀምር አይቻለሁ አሃ (2x) ስለዚህ/እኔማ አምልክሃለው ወገቤን ታጥቄ አምልክሃለው ልክህን አውቄ አምልክሃለው ልክህን አውቄ (4x)