Song Lyrics

ማራናታ

Kalkidan (Lili) Tilahun
Abetu Gulbete Hoy Ewedihalew
አዝ፦ ማራናታ (3x) ቶሎ ና የኔ ጌታ የኔ ጌታ (2x) ቃልህን በመግለጥ፧ ዓለምን ሙላና በድንቅ በተዓምር ተመላለስና አንተን ተቀብለው ነፍሳት ይዳኑና የኔ ጌታ ኢየሱስ እባክህ ቶሎ ና አዝ፦ ማራናታ (3x) ቶሎ ና የኔ ጌታ የኔ ጌታ እመጣለሁ ብለህ ቃል ገብተህልናል ቃልህ እንዲፈጸም ልጆችህ ናፍቀናል የታረደውን በግ ስለበደላችን ልናይ እንወዳለን ሁላችን በዓይናችን አዝ፦ ማራናታ (3x) ቶሎ ና የኔ ጌታ የኔ ጌታ በዕንቁ በወርቅ አርጐ እግዚአብሔር የሰራት ጥላቻ ተረስቶ ፍቅር የሞላባት ለእኛ ለልጆቹ አምላክ ያዘጋጃት ኢየሩሳሌምን መቼ ነው የማያት አዝ፦ ማራናታ (3x) ቶሎ ና የኔ ጌታ የኔ ጌታ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection