ለሰው አላወራም ምን ትርፍ አገኛለሁ ሃዘኔን ብሶቴን ላንተው እነግራለሁ ደጃፌን ዘግቼ አጫውትሃለሁ አምናለሁ ካንተ ዘንድ ምላሽ አገኛለሁ (2x) አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ ትካዜዬን ሁሉ በአንተ ላይ እጥላለሁ የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (2x) የኤርትራን ባህር ታሻግረኛለህ ከሰማያት መናን ታወርድልኛለህ ሃሳብህም ከቶ አይከለከልም ሁሉ ይቻልሃል ምንም አይከብድህም (2x) አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ ትካዜዬን ሁሉ በአንተ ላይ እጥላለሁ የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (2x) የነገሩህንም የማትረሳ ነህ አንዱም አይጠፋህም ታስታውሰዋለህ ሕመሜን በሙሉ አንተ ታውቀዋለህ መድኃኒቴ አንተ ነህ ትፈውሰኛለህ (2x) አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ ትካዜዬን ሁሉ በአንተ ላይ እጥላለሁ የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (2x) ::የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (3x)