ጣል ጣል አታርጊው ኢየሱስን ውደጂው (2x) ደግሞም አትናቂው ክብርን ለሱ ስጪው (2x) ዓይንሽ ያረፈበት እሱ ያጠፋሻል (2x) ተይ ተይ አትወላውይ ጌታ ይሻልሻል (2x) አዝ፦ ጌታ ይሻልሻል ጌታ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሃል ኢየሱስ ይሻልሃል ጌታ ይሻልሃል ነገ ዛሬ አትበል ኢየሱስን ተቀበል (2x) የሚያባብልህን ዓለምን እምቢ በል (2x) ከታሰርክበትም እርሱ ይፈታሃል (2x) ቀረብ በል ተጠጋ ጌታ ይሻልሃል (2x) አዝ፦ ጌታ ይሻልሻል ጌታ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሃል ኢየሱስ ይሻልሃል ጌታ ይሻልሃል የሚያታልለውን የሱን ቃል አትስሚ (2x) ይልቅስ ከአምላክሽ ከእግዚአብሔር ተስማሚ (2x) ሊሰርቅና ሊያድ ሊያጠፋሽ ነውና (2x) ነይ ነይ ወደ ኢየሱስ እሱን ተይውና (2x) አዝ፦ ጌታ ይሻልሻል ጌታ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሃል ኢየሱስ ይሻልሃል ጌታ ይሻልሃል እስኪ ወንድሜ ሆይ ተስፋህ ምንድነው (2x) ምንም ነገር የለ እስኪ አስበው (2x) በዚህ ክፉ ዘመን ሰብሰብ በልና (2x) አረፍ በል ተቀመጥ ኢየሱስን ያዝና (2x) አዝ፦ ጌታ ይሻልሃል ጌታ ይሻልሃልኢየሱስ ይሻልሃል ኢየሱስ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሻል ጌታ ይሻልሻል