ጐልጐታ ትመስክር ቀራንዮ ትናገር የጌታ ኃይል ጣሩን የአኳሃኑን ነገር አዝ፦ ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከኢየሱስ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከአምላኬ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከጌታ የሚበልጥ ፍቅር የለም ነፍሱን ስለእኔ የሚያሰጥ መውደድ መስቀል አሸክሞ አስጐንብሶ የሚያስኬድ የጌታዬን ፍቅር ምን ይመጥነዋል ከምንም ከምንም ከምንም ይበልጣል አዝ፦ ከኢየሱስ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከአምላኬ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከጌታ የሚበልጥ ፍቅር የለም እንዴት እንዲወደኝ እኔ የማውቀው የተወጋ ጐኑን እሱን ሳየው ነው የእሾህ አክሊል አርጐ አንገቱን የደፋው እኔን ደስ ብሎኝ ስቄ እንድኖር ነው አዝ፦ ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከኢየሱስ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከጌታ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከአምላኬ የሚበልጥ ፍቅር የለም ደም ግባት ውበትን የሌለው ተባለ ስለበደሌ ሲል ደቀቀ ቆሰለ አፉን አልከፈተም አምላኬ ዝም አለ ሕመሜን ታመመ ደዌን ተቀበለ አዝ፦ ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከኢየሱስ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከአምላኬ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከጌታ የሚበልጥ ፍቅር የለም ሀዘኔን ምሬቴን በሰፍነጉ ሞልቶ ኢየሱሴ ጠጣልኝ ከሰማያት መጥቶ ሁሉን ጨርሶታል ምንም አላስቀረም ለኔ ያስተረፈው ኾምጣጤኮ የለም አዝ፦ ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከአምላኬ የሚበልጥ ፍቅር የለም ከጌታ የሚበልጥ ፍቅር የለም ጐልጐታ ትመስክር ቀራንዮ ትናገር የጌታ ኃይል ጣሩን የአኳሃኑን ነገር