Song Lyrics

ማነው ማነው

Kalkidan (Lili) Tilahun
Abetu Gulbete Hoy Ewedihalew
በኪሩቤል ላይ የተቀመጠው በሰማይ በምድር ታላቅ የሆነው ከዙፋኑ ላይ ውረድ የሚለው እሱን ተክቶ የሚቆም ማነው አዝ፦ ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (2x) ከአምላክ በቀር አምላክስ ማነው ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (2x) ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው ውሆች በእፍኙ የሰፈረው ሰማይ በስንዝሩ የለካው በምን ምሣሌ እንመስለው ይህን እግዚአብሔር ማን እንበለው አዝ፦ ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (2x) ከአምላክ በቀር አምላክስ ማነው ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (2x) ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው ባህርን ከፍሎ የሚያሻግረው ሰማይን ከፍቶ መና የሚያወርደው በጸናች ክንዱ የሚታደገው የእስራኤል አምላክ እርሱ ብቻ ነው አዝ፦ ማነው ማነው እንደእርሱ ማነው (2x) ከእርሱስ በቀር አምላክስ ማነው ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (2x) ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው ክንዱ አይዝልም የምናመልከው ሁሌ ብርቱ ነው የማይታክተው ይሄ አምላካችን ዛሬም ሕያው ነው ተወዳዳሪ መሳይ የሌለው አዝ፦ ማነው ማነው እንዳንተ ማነው(2x) ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው ማነው ማነው እንደእርሱ ማነው (2x) ከእርሱስ በቀር አምላክስ ማነው በነፃ ብሉ ጠጡ የሚለው ዋጋ ማይጠይቅ ማያስከፍለው አንድያ ልጁን ወዶ ሚሰጠው ከእግዚአብሔር በቀር ወዳጅስ ማነው አዝ፦ ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (2x) ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (2x) ከአንተ በቀር ወዳጅስ ማነው ሁሉን ይቀርባል እሩህሩህ ነው እንደሰው አይደል አይሰለቸው ወረትን አያውቅ ጊዜ አይለውጠው እግዚአብሔር አምላክ እግዚአብሔር ነው አዝ፦ ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (2x) ከአምላክ በቀር አምላክስ ማነው ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (2x) ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection