Song Lyrics

ያላንተ ኑሮ

Kalkidan (Lili) Tilahun
Abetu Gulbete Hoy Ewedihalew
አዝ፦ ያላንተ ኑሮ አይሆንልኝም ጌታዬ አይሆንልኝም እኔስ ያላንተ አይሆንልኝም ጌታዬ አይሆንልኝም ወጣሁ ወረድኩ ብዙ አየሁኝ እንዳንተ የሚሆን መቼ አገኘሁኝ ድካሜ ሁሉ ከንቱ ነበረ አንተ ስትመጣ ሕይወቴ አማረ አዝ፦ ታዲያ ያላንተ እንዴት አድርጌ እኖራለሁ እንዴት አድርጌ ያላንተ ኑሮ አይሆንልኝም ጌታዬ አይሆንልኝም የዓለም ፍቅር ተሟጦ ያልቃል ያንተ ፍቅር ግን መቼ ያረጃል አትጠገብም ቀርቦ ላየህ አቤት ጌታዬ ምን አይነት ነህ አዝ፦ ታዲያ ያላንተ እንዴት አድርጌ እኖራለሁ እንዴት አድርጌ ያላንተ ኑሮ አይሆንልኝም ጌታዬ አይሆንልኝም የአሕዛብ ኑሮ ሁሌ ይደንቀኛል ሰው ካለ ኢየሱስ እንዴት ይኖራል አንተን ያጣ ሰው ያልታደለ ነው ከርታታ መና ተስፋ የሌለው አዝ፦ እኔስ ኑሮ አይሆንልኝም ጌታዬ አይሆንልኝም እኔስ ያላንተ አይሆንልኝም ኢየሱስ አይሆንልኝም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection