Song Lyrics

አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ

Kalkidan (Lili) Tilahun
Abetu Gulbete Hoy Ewedihalew
በዙሪያዬ ሆኖ ጠላት ሲያውከኝ ያሸነፈ መስሎ ሲፎክርብኝ በጨነቀኝ ጊዜ ወዳንተ ጮህኩኝ ሰማይን ዝቅ አርገህ ከተፍ አልክልኝ አዝ፦ አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (2x) እጆቼን አንስቼ ተገፍ አልኩኝ እግዚአብሔር ከሰማይ ተበቀለልኝ ምድር ተናወጠች ቁጣውም ነደደ በጠላቶቼ ላይ መብረቅ አወረደ አዝ፦ አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (2x) እግሮቼም ቆሙልኝ አልተንሸራተቱም ጠላቶቼን ያዝኩኝ አላመለጡኝም በኮረብቶቹም ላይ ለሚያቆመኝ ጌታ እስኪ ላመስግነው ልዘምር በእልልታ አዝ፦ አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (2x) ለሚታመኑበት እርሱ ጋሻ ነው ክፉዬን አይወድም ይነዳል ቁጣው ከመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ይሰማኛል እግዚአብሔርን አይቶ ጠላቴ ፈርቶኛል አዝ፦ አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (2x) አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ አቤቱ የኔ ጌታ እወድሃለሁ እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection