ገና ከጅምሩ በዚህ ሂድ ያለኝ ወጥቼ እስክመለስ ዐይን ዐይኔን ያየኝ ጥርሴ እየሳቀ ልቤ እያለቀሰ የኖርኩበት ዘመን በክብር ተካሰ (2x) አዝ:- አባት ብለው አይገልጸውም ወዳጅ ብለው አይገልጸውም ረዳት ብለው አይገልጸውም ኧረ እኔስ ማን ልበለው (4x) ገዳዬ እንዳያየኝ እጁ ላይ ተኝቼ ደጅ አድሬ አላውቅም ከእቅፉ ወጥቼ (2x) እዩ አባት (2x) ነፍሱን እስከመስጠት (2x) መንገዴን አጥሮታል ዙሪያዬ ግድግዳ እረ እንዴት ጭንቅ ነው የመከራው ናዳ (2x) ከቤት ውስጥ ትንሽ ነኝ ዘመድ የለኝ ደግሞ የአለእድሜዬ ክብር አሳየኝ አቁሞ (2x) አዝ:- አባት ብለው አይገልጸውም ወዳጅ ብለው አይገልጸውም ረዳት ብለው አይገልጸውም ኧረ እኔስ ማን ልበለው (4x) ቀን ይማከራሉ ሌሊት ያደባሉ ህልም የነገርኳቸው አብረውኝ የበሉ ወንድሞች ተባሉ ሄጄ ሂጄ ደክሞኝ መንገድ ላይ ወድቄ ደግሞ እንዳይገድሉኝ በእጁ ትደብቄ እዛው ተደብቄ እዩ አባት (2x) ነፍሱን እስከመስጠት (5x)