Song Lyrics

እድለኛ ነኝ

Kaleab Tsegaye
Endihim Ale
አዝ:- እድለኛ ነኝ እኔ (2x) እድለኛ አዲስ እድሜ ከሰማይ የሰጠኛ ነኝ እኔ እድለኛ እድለኛ ነኝ እኔ አዲስ እድሜ ከሰማይ የሰጠኛ ለአምልኮ ማን ይቀድመኛል መስቀሉ ለእኔ ነው የተሰራልኝ ስሞት ህዝብ ሊያየኝ ሊሳለቅብኝ ለካ ተዐምራት በጣም የሚያምረው እግዚአብሔር ከሰማይ ሲያረፋፍድ ነዉ ባልጠፋ ሰዓት በሌሊት ተነስቶ ያገላብጥ ጀመር መዝገቤን ጐትቶ የፋርስና ሜዶን ህግ ተገልብጧል ሃማ መሞቻዉን አሳምሮ ሰርቷል የሚሞተውን ሰው አትሞትም ብሎታል የመኖሪያ ፈቃድ ኢየሱስ ሰጥቶታል በእርሱ እድሜ አይቀለድም (4x) በራዕዩ ምክንያት ጉድጓድ ውስጥ ቢጣልም እግዚአብሔር አላለም መንገድ ላይ አይቀርም መቼ ጓዳ ቀረ በጉድጓድ ተውጦ አደባባይ ወጥቷል ነገር ተገልብጦ በግብጽ በአካባቢው በአገር ሰው እያለ ተሸጦ የመጣው ዙፋን ላይ ቁጭ አለ ፈርኦን በቤቱ ቢኖርም ባይኖርም ጌታ ንጉሥ ካለህ መሾምህ አይቀርም አዝ:- እድለኛ ነኝ እኔ (2x) እድለኛ አዲስ እድሜ ከሰማይ የሰጠኛ ነኝ እኔ እድለኛ እድለኛ ነኝ እኔ አዲስ እድሜ ከሰማይ የሰጠኛ ለአምልኮ ማን ይቀድመኛል (2x) እድለኛ ነኝ እኔ አዲስ እድሜ ከሰማይ የሰጠኛ ለአምልኮ ማን ይቀድመኛል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection