Song Lyrics

ሰይጣን ውሸቱን ነው

Kaleab Tsegaye
Endihim Ale
ፀሐይ ዘምበል ብላ አመሻሹ ላይ ነኝ ችግሬ እያለ ሚነጋ መሰለኝ ለካ አምላኬ ሰምቷል ጠላቴ እየዛተ የተዘጋጋው በር አውቆ ተከፈተ አዝ:- ሰይጣን ውሸቱን ነው (2x) ትሞታለህ ያለው (2x) ኢየሱስ እውነቱን ነው (3x) አትሞትም ያለው (2x) በሞትና በእኔ አንድ እርምጃ ቀርቶ ምን ረዳኝ አትበል ከረፈደ መጥቶ አምላክህ ሲነሳ ሲያንጐዳጉድ ከላይ መከራህ በጓዳ ክብርህ በአደባባይ ይደርደር ይደርደር በገና ዕድሜ ቀጠለልኝ ይገባዋልና ሌላ ሌላ ምሥጋና (4x) ፈሮን ከሁአላ ቀይ ባሕር ከፊት ነው ግብጽ አይመለሱም ኢየሱስ ኢየሱስ ብለው በአራቱም አቅጣጫ ሞት እየቸኮለ የገዳዬ ገዳይ ከሰማይ ብቅ አለ አዝ:- ሰይጣን ውሸቱን ነው (2x) ትሞታለህ ያለው (2x) ኢየሱስ እውነቱን ነው (3x) አትሞትም ያለው (2x) ይደርደር ይደርደር በገና ዕድሜ ቀጠለልኝ ይገባዋልና ሌላ ሌላ ምሥጋና (4x) (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection