ቢሆንም ባይሆንም አምልኮዬን አላቆምም (2x) አዳዲስ መዝሙር ለእርሱ ነውና (ምሥጋና ምሥጋና) ለታላቅነቱ (ምሥጋና ምሥጋና) (2x) ታሞ አዘነ ሞቶ አለቀሰ የሰው እርዳታ መች ከዚህ አለፈ ሲታመም ቀርቶ ሞቶ ቢደርስ ሬሳ አይተናል ሲቀሰቀስ ቢሆንም ባይሆንም አምልኮዬን አላቆምም (2x) የቤቱን ትልቅ ኤልያብን ትቶ ቀቡልኝ ካለ እረኛውን ጠርቶ ያዕቆብን ወዶ ኤሳውን ከጠላ ሲረፍድ ይገባል የጌታ ስራ ትክክል ነው ትክክል ነው (6x) የሰማይ መስኮት ቢከፈት እንኳን በአንድ ቀን ይሄ እንዴት ይሆናል ንጉሡ እምቢ ቢል ትንቢት አዳምጦ ሳይበላ ሞተ በሰው ተረግጦ ቢሆንም ባይሆንም አምልኮዬን አላቆምም (2x) አዳዲስ መዝሙር ለእርሱ ነውና (ምሥጋና ምሥጋና) ለታላቅነቱ (ምሥጋና ምሥጋና) (2x) ትክክል ነው ትክክል ነው (6x)