አይሁዶች ሃሳባቸው በሃማ እጅ መጥፋታቸው (2x) ማን እንደሚሞት ላልታወቀ መስቀያው ተሰርቶ አለቀ ጆሮውን ለሰማይ ሰጥቶ የምድሩን ለሃማ ትቶ ከአባቱ ያዳመጠ ያው በክብር ተገለጠ የሰማው ከላይ ነው (3x) የሰማው ከላይ ነው (3x) አዝ:- ሰሞኑን ሰማሁ ክፉ ወሬ በተወለድኩበት በአገሬ ትንሹ ዮሴፍ በሕይወት አለ አባትዬው ሰምቶ ጉድ አለ እረ እኔ አልሞትኩም አለሁ እረ እኔ አልሞትኩም (3x) ይሄ ነው ተነስ ቀባው የኔን ልብ ያሳረፈው (2x) ነብዩ ቀብቶት ወጣ ቅባቱ ነገር አመጣ ከጐልያድ ጭንቅያሳረፈውን መልሶ ጠላት ሆነዉ የእግዚአብሔር ቃሉ አልፈረሰም ሳኦል ሞቶ ዳዊት ነገሠ የሰማው ከላይ ነው (3x) የሰማው ከላይ ነው (3x) አዝ:- ሰሞኑን ሰማሁ ክፉ ወሬ በተወለድኩበት በአገሬ ትንሹ ዮሴፍ በሕይወት አለ አባትዬው ሰምቶ ጉድ አለ እረ እኔ አልሞትኩም አለሁ እረ እኔ አልሞትኩም (3x) ስኬቴ ያስከፋቸው ውድቀቴ ደስ ያላቸው (2x) ላልሞተ ሰው አስለቅሶ በቁሜ አፈር አልብሰው ልብ ሊስቅ እንደለመዱ ለታይታ ሙሾ ወረዱ ከሰማይ በቃቹህ አለ ለዘሩት ዋጋ ከፈለ የያዘኝ እጁ ነው (3x) የያዘኝ እጁ ነው (3x) አዝ:- ሰሞኑን ሰማሁ ክፉ ወሬ በተወለድኩበት በአገሬ ትንሹ ዮሴፍ በሕይወት አለ አባትዬው ሰምቶ ጉድ አለ እረ እኔ አልሞትኩም አለሁ እረ እኔ አልሞትኩም (3x)