ካንተ የበቀልሁ ካንተ የተገኘሁ ህይወትህ ያለብኝ ባንተ የምኖረው ፍሬ የማፈራው የምለመልመው ምንጩ አንተ ስለሆንህ ከአንተው/ ከራስህ ነው 2X ካንተው ላንተው አቅሜም አንተው ካንተው ላንተው ፀጋውም ያንተው ካንተው ላንተው ስጦታው ያንተው ካንተው ላንተው ክብሩም ላንተው ራሴን ብሰጥህ ቀድሞም ያንተ ነበር መልሰህ ውሰደኝ በሠራኸው ክበር መላ እኔነቴን እንዳሻህ አድርገው ፈቃዴን መስጠቴም ሲያንስህ ነው 2X ካንተው ላንተው አቅሜም አንተው ካንተው ላንተው ፀጋውም ያንተው ካንተው ላንተው ስጦታው ያንተው ካንተው ላንተው ክብሩም ላንተው