Song Lyrics

የኔ ውድ

Yene Wud

እርሱ ነው ጥሜን ያረካ ውሃዬ መብል የነፍስ ማቆያዬ እውነተኛ ፍስሃዬ እርሱ ነው ሃዘን መከልከያዬ የማካፍለው ደስታዬ ልዩ የሆነው ሰላሜ በምድር ያለ ሁሉ ቢጠራ አንድ ላይ ብደምረው እንኳንስ ዓይኔ ሊገባ ቀልቤን ለአፍታ ሊወስደው ከኢየሱስ ሲተያይ ሁሉ ነገር ዜሮ ነው በብዙዎቹ መሃል የእኔ ውድ ብቻውን ነው እርሱ ነው በበረሃ መሃል ገነቴ በፈተና ሁሉ ፅናቴ በድቅድቅ ጨለማ መብራቴ እርሱ ነው የቆምሁበት መሠረቴ የዘለዓለም ቤቴ ዋስትናዬ ትምክህቴ እርሱ ነው ከዓለም የለየኝ ቅጥር የተሸነፍሁለት ፍቅር ሁሉን የሚያስንቀው ክብር እርሱ ነው ከሃጢአት የዳንሁበት ፈውሴ ምተማመንበት ዋሴ አብ ፊት የምቀርብበት ልብሴ በምድር ያለ ሁሉ ቢጠራ አንድ ላይ ብደምረው እንኳንስ ዓይኔ ሊገባ ቀልቤን ለአፍታ ሊወስደው ከኢየሱስ ሲተያይ ሁሉ ነገር ዜሮ ነው በብዙዎቹ መሃል የእኔ ውድ ብቻውን ነው ብቻውን ነው ውዴ ውዴ ኢየሱስ ብቻውን ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection