Song Lyrics

አባል አይደለም

ዝም ያለ ዜማ መልእክት የሌለው ለብ ጭጭ ያለ ጣዕም ወይም ምሬት የሌለው ላርገቡት የሚነድ ለለኮሱት የጋየ ድቅል ድብልቅ ፍቅር ለምን እንደሚኖር ያላየ ልክ የማይጠይቅ እዉነትን አርቆ የጣለ ከተከተተበት የማይዝል ግርዶሽ አድማሱ የሆነ መንጋው ሁሉ ተለያይቶ ወደ ገደል ስጠብቅ ተራ የሃይማኖት ካራ ጨብጦ እግዜር የኔ የኔ የኔ ይባላል እግዚአብሔር አባል አደለም እግዚአብሔር ድርጅት የለውም የኔ ነው ባለ መቼ ሆነ መፅሐፉ ይህን አላስተማረ መዳኔ አዳኝ ስጦታ ነው ቃል የገባው ለሁሉ ነው በልጁ በኩል ላገኘው አዳኝ አምላክ አባት ሚሆነው በእርሱ ስራ ምክንያት እንግድነት የተሻረልን መፃንነታችን ቀርቶ ባላገሮች የሆንን እርቀን የነበርን ከቅርቦቹ ተዋህደን አንድ ሆነን ከተፈጠርን ለስልጣን ጥም ብሎ ህዝብን ከህዝብ መለያየት ትምርተ ልዩ እያሉ ራስን አግንኖ ማየት ለሰነፍ ጧሪ ክምችት ቤተስቡ ቢጓተት ቢጣላ የሚከፍል ይጠየቃል ኃዋላ የጥንቱ ነኝ አንባቢም ነኝ ዓለም አቀፍ ነኝ አይሰራም የፀጋ ነኝ የትጋት ነኝ የእምነት ነኝ አይሰር አይሰር አይሰራም እግዚአብሔር አባል አደለም እግዚአብሔር ድርጅት የለውም የኔ ነው ባለ መቼ ሆነ መፅሐፉ ይህን አላስተማረ ስጦታ ነው ቃል የገባው ለሁሉ ነው በልጁ በኩል ላገኘው አዳኝ አምላክ አባት ሚሆነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection