Song Lyrics

ስሜ ነው

Sime New

የአረማመዴን ጥድፊያ ያየ ጥበብ እንዳጣሁ ያስተዋለ የስህተቴን መብዛት አይቶ መጨረሻዬን ደመደመ "እርግጥ ነው ይወድቃል" አለ ችኮላዬ ለጥፋት ስለነበረ ማን ነበር ለመካሪ ያስቸገረ እንደእኔ ያለ ነገር ግን ፍፃሜዬን ቀየርከው ፍቅርህ እጅግ ድንቅ ይቅርታህን በህወቴ ገለፅከው ያየኝን ሁሉ ገረመው መልካምነትህ መጠርያዬ ሆነ ስምህ በቅኖች ተመሰገነ ታሪክ እንደምትቀይር ታመነ ወድቆ የነበረው ሰው ቆመ አንስተኸኛልና ስለአንተ አወራለሁ ደግፈህ ስላቆምከኝ ዛሬን አይቻለሁ ከፍቅርህ የተነሳ ሙሉ ሰው ሆኛለሁ የሚያውቀኝ ሲያየኝ ሌላ ቃል የለውም "ጌታ መልካም ነው" ነው የሚለው እግዚአብሄር መልካም ነው ስሜ ነው ራሴን በራሴ ልጎዳ ስንት ጊዜ ሞከርኩ መንገዴ ላይ ስንት ጊዜ ቆምህ ስንቴ በእጅህ ተከለከልሁ ሞቴን ተንፍሼው አውቃለሁ እረፍቴን ፈልጌ አጥቼዋለሁ ስንት ጊዜ ተስፋ ቆርጫለሁ አሁን ግን በፍቅርህ ታድሻለሁ እውቀቴ አልጠበቀኝም ማስተዋሌ አላዳነኝም ፍቅርህ ጠንካራ ምሽግ ሆኖኝ በአንተ ስንቱን አመለጥሁኝ ይህ ሁሉ ሲሆን የነበረ ከምን እንዳተረፍከኝ ያየ ባሰበኝ ቁጥር ተደነቀ መልካምነትህን አወቀ አንስተኸኛልና ስለአንተ አወራለሁ ደግፈህ ስላቆምከኝ (ኡሁሁሁሁ ) ከፍቅርህ የተነሳ ሙሉ ሰው ሆኛለሁ የሚያውቀኝ ሲያየኝ ሌላ ቃል የለውም "ጌታ መልካም ነው" ነው የሚለው እግዚአብሄር መልካም ነው ስሜ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection