ድምፅ በዝቶናል ብዙ መገለጥ አለ ጠቢብ በዝቶናል ዕውቀት ለሁሉ ታደለ ሁሉ መካሪ ሁሉ አስተካካይ ግንድ ይዞ የሚዞር ጉድፍ ገላጋይ ከፍቅር ያልሆነ ማቅናት ያልመራው ግብ ለማስቆጠር ብዙ የሚለፋው አንተ ግን ከፍቅር እውነት ተናግረህ የጠፋውን ነፍስ ትመልሳለህ አንተ ተናገር ዝም ይበል ሁሉ ልብ ተይዞ በዚህ ዓለም ከንቱ ስጋ በዛብን ከንቱ ጩኸቱ ምን ፊደል ቢያምር ቃል ከጥሩ ቃል ቢሳካ በምድር ውሃ ነፍስ ፈፅማ አትረካ ቀሚስ ቢረዝም ጸሎት ቢያስገርም የጠቢባን ቃል ነፍስ አያክምም ህይወት የሚሰጥ ህይወት የሆነው መንፈስ የሚጠልቅ ቃልህ ብቻ ነው አንተ ተናገር ዝም ይበል ሁሉ