በነውጥ ቢሆን በእርጋታ በተራራም በዝቅታ በማግኘትም ወይ በማጣት በልጅነት እንዲሁም በዕውቀት ነፍሴ አትረሳም አንድ ነገር ውዱ ሆናለች የ እግዚአብሔር ምንም ቢፈጠር ምንም ቢመጣ ከቶ አልችልም ከእጁ ልወጣ ተወድጃለሁ በቃ ተወድጃለሁ ተወድጃለሁ በቃ አምላክ ወዶኛል አምላክ ወዶ አምላክ ወዶ አምላክ ወዶኛል ፍቅሩ ራሱ እንደሰው አይደለም ሲዛመደኝ ክብሬን አላለም ዕዳዬንም ራሱ ከፍሎታል እንዳለሁኝ ተቀብሎኛል የምታየው እርሱ ራሱ ልብሴ ሆኗል ህያው ንጉሱ አንድ አካል ከአምላኬ ክብር ሰጠኝ ልክ አጣ ልኬ ተወድጃለሁ በቃ ተወድጃለሁ ተወድጃለሁ በቃ ኢየሱስ ወዶኛል አምላኬ ወዶኛል /8x ተወድጃለሁ በቃ ተወድጃለሁ ተወድጃለሁ በቃ ኢየሱስ ወዶኛል