Song Lyrics

ህይወት ሆኖልኛል

ከህይወት ገበታ እንድቆርስ አደለኝ ነፍሱን ለእኔ ከፍሎ ለደስታ ህይወት ለየኝ በወጣልኝ ዕጣ መኖር አገኘሁኝ በሚታይ መብለጤ ዓለምን ናቅሁኝ ባርያ ሆኜ ሳለሁ የኃጢአት ባለዕዳ ሰይጣን አሸክሞኝ የዘመን አበሳ ነገር ግን ነፃነትህ በሬን ከፍቶ ገባ በተራ አይደለም በዘለዓለም ጌታ ህይወት ሆኖልኛል ነፃ አውጥቶኛል ለእኔ ሞቷልና አቀርባለሁ አምልኮ ምስጋና ዘመን ያወፈረው ያሰረኝ ሰንሰለት መመረጤን ሲያየው ወደቀ ከመሬት ልከፍለው አይደለም የሠራልኝ ለእኔ ነፃነት በነፃ መጥቷል አጠገቤ ይሄ ብቻ አይደለም አለኝ የተሠራ የሚያስረሳኝ የዚህን ዓለም መከራ መኖሪያ ሚሆነኝ ዘለዓለም በተድላ የሰው ዓይን ያላየው በእጅ ያልተሠራ ህይወት ሆኖልኛል ነፃ አውጥቶኛል ለእኔ ሞቷልና አቀርባለሁ አምልኮ ምስጋና ይበራል ጨለማው አይቆምም ከፊቴ አይደለሁም ምንም ይታያል መብራቴ አምላክ ጎጆዬ መጥቶ በቃሉ ያናገረኝ የዘለዓለም ህይወት ሞቶ የሰጠኝ እኔ ነኝ ህይወት ሆኖልኛል ነፃ አውጥቶኛል ለእኔ ሞቷልና አቀርባለሁ አምልኮ ምስጋና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection