Song Lyrics

ይችላል

አቅሜን ሁሉ የጨረሰ ጊዜአትን ተሻግሮ የደረሰ ልላቀቅ ያልቻልሁትን ነገር ከላዬ የሚያወርድ የሚጥል አምላኬ ሁሉን ይችላል ጌታዬ ሁሉን ይችላል ሁሉን መቻል ነው ማንነቱ የሚያቅተው የለም ክንደብርቱ የሌለን ወደ መኖር ያሻገረ በተአምር በትንሳኤ የከበረ የህዝቤን ዕንባ የሚያብስ አስጨናቂውን የሚያፈርስ ፍትህ ከሰማይ የሚያመጣ ጉልበተኛውን የሚቀጣ በቁርጥ ሰዓት እየተገኘ በማዳን ሥራው ስሙ የናኘ ሁሉን እንቢ ያለውን ነገር ለጌታ ቀላል ነው መቀየር ኢየሱስ ሁሉን ይችላል ጌታዬ ሁሉን ይችላል አምላኬ ሁሉን ይችላል ጌታዬ ሁሉን ይችላል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection