Song Lyrics

እየወደድሁህ መጣሁ

መልካም ስለሆንህ የማያስረዱት ዓይነት በመከራዬ ውበት ሸመትሁበት ምትገርም ስለሆንህ የማያባራ ዓይነት በውድቀቴ ፍቅርህን ቀመስሁበት ሁሉን ተጠቀምህበት ሁሉ ወደዚህ አመጣኝ እንዳያጠፋኝ የሰጋሁት ይበልጥ ወዳንተ አስጠጋኝ ፍቅርህ ልቤ ደረሰ መወደድ ራሴን ተሰማው ህይወቴ ህይወት ቀመሰ ብርሃንህ ቀኔን አበራው እየወደድሁህ መጣሁ እየወደድሁህ ፍቅር ስለሆንህ እንዳንተ ብቻ ዓይነት ከእውነት ጋር ተስማማሁ በምህረት አባት ስለሆንህ ኢየሱስ ያለው ዓይነት ሳልጠይቅህ አወረስኸኝ ብዙ ንብረት እንዴትም ሊገኝ ማይችል ውዱን በነፃ ሰጠኸኝ ጠላትነቴ ተሽሮ አካልህ ነው ያደረግኸኝ አካሄዴን ቀይረሃል ከፍቅርህ ሸክም በኇላ ዛሬ እንደትናንት አልፈዝም ለዓለም ብርቅ ተላላ እየወደድሁህ መጣሁ እየወደድሁህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection