አምላክ ሆነህ ሳለህ ለእኔ ብለህ እኔኑ ሆንህ በቃላት ማይገለጥ ክቡርነትህን ለፍቅር ተውህ ራስህን ባዶ አረግህ (ትሁቱ) ለመስቀል ሞት የታዘዝህ (ምትኬ) መስዋዕት አንተ ሆነህ (የ እግዚአብሔር በግ) ካህኑም አንተ (ሊቀ ካህን) ከአብ ታረቅሁኝ ፍቅርህ ይገርመኛል /2x ፍቅርህ ይደንቀኛል /2x የተሠጠኝ ህይወት ተመን አልባነት ቢሠወረኝ ሥጋዬ አስቸግሮኝ ከሩጫዬ ቢያዘገየኝ በድካም ምትራራ (ምትታገስ) ትሁት ጠበቃ ስላለኸኝ (ጌታ ኢየሱስ) (አ ሃ ባንተ ምክንያት ሁሌ ፀናለሁ) ተስፋዬ ይታደሳል (ታማኝ ነህ) ከቶ ላትተወኝ ( ለዘለዓለም) ስለያዝኸኝ ትዕግስትህ ይገርመኛል ያላንተ ማን ይችለኛል ይቅርታህ ይደንቀኛል ሰው ቢሆን ድሮ ጥሎኛል ፍቅርህ ይገርመኛል / 4x ይገርመኛል ፍቅርህ ይደንቀኛል ፍቅርህ