Song Lyrics

ምራኝ

Mragn

ምራኝ መንገድ አሳየኝ ባስቸግርህ የማትለየኝ ጉልበቴን ለፈቃድህ አበርታ ብቻዬን መጓዝ አልችልም ለአፍታ ህይወት ዝብርቅ እያለ ሰው ምርጫውን ከተከተለ በማስተዋሉ የተደገፈ በራሱ ምኞት ተጠለፈ ከአዕምሮ ባለፈ በምክርህ ግን የተደገፈ ሁሉ በፈተና ሲጠልል እርሱ ብቻ ፀንቶ በድል አለፈ እኔም ይህንን አውቄ ትምክህቴን አውልቄ በእራስ ከመተማመን ትምህርት ርቄ ምንጬን ፈልጌ መጣሁኝ ብቻዬን ስለፈራሁኝ መጥቼ አንተ ውስጥ ገባሁኝ ምራኝ መንገድ አሳየኝ ባስቸግርህ የማትለየኝ ጉልበቴን ለፈቃድህ አበርታ ብቻዬን መጓዝ አልችልም ለአፍታ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection