Song Lyrics

ኑሮ

Nuro

ችላ አልልም መመረጤን አላራክስ ውድ ህይወቴን አመፅ አይሆንም ምልክቴ እምነቴ ህያው ነው በድርጊቴ ክብር ስላለኝ ለመጠራቴ ቸልታ አይነግሥም ቤቴ በጸጋህ ከመደነቄ የተነሳ ምኞቴን ስተው አልሳሳ አዲስ ዘር ውስጤ ስላለ የማይቻል ኑሮ ለእኔ ቀለለ በማዳንህ ደስታ ስለረካሁ የጥፋት ሩጫዬን ፈቅጄ ገታሁ ይህ ዓለም አንተን እንዲያውቅህ በመኖር ልዩነት ልግለፅህ ብርሃን ልሁን በብርሃንህ በአንተው ህይወት ላክብርህ እየተቆረስሁ ባስቻልኸኝ ሁሉ ያጡ የጎደሉ እንዲሞሉ በአንተ ከመኖሬ የተነሳ ስምህ በደግ ይነሳ ለመፈቀሬ ካለኝ ክብር ሥጋን ማቅበጤ ይቅር በጸጋህ ከመደነቄ የተነሳ ኮተቴን ስጥል አልሳሳ ልንፃልህ ይጥራ መልኬ ላፍቅር እንዳምላኬ ትረስርስ ትሙላ ነፍሴ ይሰልጥን መንፈሴ እስክትመጣ እስካገኝህ በአካል እስክንተያይ በገባኝ መጠን ልኑር ልሁን ትጉ አገልጋይ ክብር ስላለኝ ለመጠራቴ ቸልታ አይነግስም ቤቴ በጸጋህ ከመደነቄ የተነሳ ዓለምን ስተው አልሳሳ ለመፈቀሬ ካለኝ ክብር ሥጋን ማቅበጤ ይቅር በጸጋህ ከመገረሜ የተነሳ ምኞቴን ስጥል አልሳሳ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection