Song Lyrics

በረታሁ

Beretahu

ከመኝታዬ ስነሳ ማለዳ ከአልጋዬ ስወርድ ትናንት እንቅልፍ ከነሳኝ ከሃሳብ ጓዜ ጋር ልነጉድ የየዕለቱ ምግቤን ምህረትህን አቃልዬ ደግሞ ነጋብኝ አልሁኝ አንተው ላይ ፊቴን አጥቁሬ ያልታዘዘልኝ ሸክም በጣም ስለተጫነኝ ይህ መያዣ የሌለው ክብደት እንዳጎበጠኝ አዋለኝ ሸክሜ እጅግ አስጎንብሶኝ ማየት ስለተሳነኝ ካገኘሁት ስላተም ስነጫነጭ አዋለኝ እቤቴ በግዴ ገባሁኝ አልጋዬ ላይ ቁጭ አልሁ በጸጋህ ብርታት ነቃሁ ቃልህን አነሳሁ አቅሜን ተረዳሁ በእኔ ጣለው ስትል ሰማሁ በድንገት እርፍ አልሁ የከበደኝን ሁሉ ጣልሁ በረታሁ! በእጅህ በመንፈስ በኃይል በረታሁ! ከእንቅልፌ ስነቃ ስጀምረው ቀኔን አዲሱን ትናንት በእርዳታህ የተወኝ ዳግም ተነሳ ሊያደርግ ልማዱን የየዕለቱ ምግቤን ፍቅርህን አጣጥሜ እሰይ ነጋልኝ አልሁ ጭንቀቴን በአንተ ጥዬ ትናንት ያጎበጠኝን እረፍት ያሳጣኝን ሁሉ ከአዕምሮዬ ወሰድኸው ሰላም ሞላኸኝ በምትኩ አንተ የሰጠኸኝ ሰላም አዕምሮዬን ስላለፈ ፈገግታዬ ደመቀ ደስታዬ ለሁሉ ታወቀ ደስታዬ የገረማቸው ጥያቄ ፈጥሮባቸው አልዋጥ አላቸው ለውጤ ሰላሜ ታዬ ከውስጤ ሚስጥሬን ገለጥሁ እንዲሁ ሰላም ለተጨነቀ ሁሉ ምንጩ ከላይ ነው በነፃ ሸክምን ከትከሻ የሚያነሳ ህይወቴ በሠሪው እጅ ነው ጉዳዬ ያለው እግዜር ቢሮ ነው ህይወቴ በሠሪው እጅ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection