Song Lyrics

አለ ኑር

Alle Noor

አለማመን ሲታመን መናኝ ተጓዥ ሲጠፋ ዓለም ጨርቋን ስትጥል ሁሉ ለባዶ ሲለፋ እውቀት ትዕቢት ሲሆን ጥበብ መጀመሪያው ሲገፋ ሞኝ መባልን ምረጥ ተያይዘህ እንዳትጠፋ እግዜሩ አለ በል በኑሮ ስብከቱማ አዝሏል የሁሉን ጆሮ እውነት የመኖር ክብደት ከሌለው ንግግርማ ቀላል ነው ያላዩት ብርሃን ይታይህ ቀንህ ለአንተ ይታዘዝ በቀደዱልህ እንዳትሾልክ አጥሩን ገንጥለህ እለፍ ፍቅርን መኖር ከሞከርህ እውነትን ዕድል ከሰጠኸው የለም ያሉትን ያዩታል ወኪል መሆን ይሄ ነው እግዜሩ አለ በል በኑሮ ስብከቱማ አዝሏል የሁሉን ጆሮ እውነት የመኖር ክብደት ከሌለው ንግግርማ ቀላል ነው ልለይ ከከንቱ ማይጠቅም ሁካታ ከሚያደነዝዝ አልፍቶ የሚያሳጣ እርካታ የአምልኮን መልክ ይዤ አልቅር በመንፈስ ደንዝዤ ጩኸት ያለበትን ስከተል ጎድዬ አልቅር ከቁም ነገር እውነት ምንድነው ርምጃዬን ካልወሰነ ሃሳቤን ካላረቀ በስልጣኑ ካልበየነ እንዲሁ ለመልክ ስምህን ከምጮኸው የእውነት ልወቅህና አለመታዘዜን ጣለው ስበረው ከልብ አውቄህ ከልብህ መኖር ልጀምር ፍጥረት ይህንን አይቶ ፍቅርህን አብሮኝ ይዘምር ከንቱነትን ሳሳድድ ዘመኔ ከሚያልቅብኝ ዝናውም ዕውቅናውም መድረኩም ሁሉም ይሂድ ይቅርብኝ እግዜሩ አለ በል በኑሮ ስብከቱማ አዝሏል የሁሉን ጆሮ እውነት የመኖር ክብደት ከሌለው ንግግርማ ቀላል ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection