የሰው ዘር ጠምቶኝ ነበር ብቸኝነት ቤቱን ተክሎብኝ ሃዘን ትካዜዬ አይሎ ልቤን መሸከም ከብዶኝ ነበር እህህ ነበር ቋንቋዬ አቀበት ሆኖ ኑሮዬ አንገላቶኝ ነበር ሰልፌ አፋኝ ወጥመዴን ታቅፌ ችግሬን ያዩ ሁሉም ሲሸሹ ምን እንሁን ያሉኝ ደርሰው ሲጠሉኝ የቅርቤ ያልሁት ሰው ሁሉ ሲቀየር ግራ ገብቶኝ ነበር ከፍጡራን መፍትሄ ጠብቄ በውጤቱ ግን ደንግጫለሁ ሁሉ ከላይ ሲመለስ ውስጤ የደረሰው እጅህ ነው ተመልክቶሃል ጉድለቴ አሳስቦሃል ጭንቀቴ ጉዳይህ ሆኗል ጉዳዬ ቁም ነገር አለህ ከህይወቴ /2x ለማስታገሻ የወሠድኳቸው ደዌዬን አብሰውት ነበር ፍቱን መድኃኒቴን ባላገኝህ ህመሜ ጨርሶኝ ልቀር በመጨረሻ ዞሬ አንተ ጋር መጣሁ ከዚያ ችግሬን ሁሉ አጣሁ የነፍሴን እንቆቅልሽ ፈታህ በፍቅርህ የሃዘኔን ጅረት ገታህ ተመልክቶሃል ጉድለቴ አሳስቦሃል ጭንቀቴ ጉዳይህ ሆኗል ጉዳዬ ቁም ነገር አለህ ከህይወቴ /2x እንዴት ይረሳል?! /2x ሁሉ ትቶኝ ሲሄድ ወዳጅ ሆነኛል እንዴት ይረሳል?! 2x ጠፍቼ ነበርሁኝ አግተኸኛል እንዴት ይረሳል?! 2x ከሞተው ህይወቴ ማር አውጥተሃል እንዴት ይረሳል?! 2x ሙላቴ ሆነኸኝ ደስታ አጥግበኸኛል ተመልክቶሃል ጉድለቴ አሳስቦሃል ጭንቀቴ ጉዳይህ ሆኗል ጉዳዬ ቁም ነገር አለህ ከህይወቴ /2x