ራሴን ተደግፌ ልቆም ለረጅም ጊዜ ጣርሁኝ በእያንዳንዱ እርምጃዬ በየጥጉ ወደቅሁኝ ለመጠገን እንዳልመች ደቅቄ ተሠብሬአለሁ ህይወት እጁን ጨብጦ ጡጫው ፊቴን ነው ያገኘው የማማክራቸው ሁሉ የሌለ ጤንነት ይሰብኩኛል ምናልባት ትንሽ ቢሰሙኝ ከችግሬ ጥቂት ይረዱኛል ህይወቴ አዘምሞ መሬት ሊነካ ሊወድቅ ጥቂት ነው የቀረው እንዲያም ሆኖ የተሸከመው ብዙ የሰው አደራ አለው ጌታ ሆይ ገፅታዬን ስገነባ ዕንባ እና ድካሜን ውጫለሁ ከዚህ በላይ ልፈነዳ ነው ራሴን ጸጋህ ላይ ጥያለሁ አርፋለሁ በጸጋህ አርፋለሁ በእጅህ አርፋለሁ በጸጋህ /2x በሠራ አካሌ ሁሉ እሣት የሞላ ይመስለኛል ከውስጤ የሚወጣውን ህመም መታገስ አቅቶኛል በደምሥሬ የሚዞረው እሾህ ሆኖ ይሰማኛል የገዛ ሥጋዬ እንኳ እንቅልፍ የለሽ ጠላት ሆኖብኛል ፈተና ግሳንግሱን እንደያዘ እንደ ጎርፍ በላዬ አለፈ ዕንባዬ ፈሶ ፈሶ ደረቀ ጥንካሬዬ ሁሉ አለቀ ህይወቴ አዘምሞ መሬት ሊነካ ሊወድቅ ጥቂት ነው የቀረው እንዲያም ሆኖ የተሸከመው ብዙ የሰው አደራ አለው ጌታ ሆይ ገፅታዬን ስገነባ ዕንባ እና ድካሜን ውጫለሁ ከዚህ በላይ ልፈነዳ ነው ራሴን ጸጋህ ላይ ጥያለሁ ይሻለኛል ጸጋህ ይሻለኛል እጅህ ይሻለኛል ጸጋህ /2x ሃሳቤ ይታመን እምነቴ ይብዛ ነፍሴ ትገዛ ፍቅርህ በእኔ ይታወቅ እግሬ መንገድህን ይዛ አንተ እኔን ብለሃል ማን ይከለክልሃል ማን ይቃወምሃል?! ፍጥረትን ባበጀ ሁሉን ቻይነትህ ዕዳዬን ወስደሃል