አንተ ታላቅ ነህ ከሁሉ የበላይ እኔ ግን ትንሽ ነኝ በጣም ከሩቅም አልታይ ከትልቅነትህ ብዛት አላውቅህም ነበር ግን ፍቅር ነህ ሳትንቀኝ ልጅህ አደረግኸኝ አመሰግናለሁ ፍቅርህ ዘለዓለም ነው አመሰግናለሁ ቃል አጥሮኝ ነው /2x ደካማ ነበርሁኝ ስንፍና የተጫነኝ ትዕግስትህ ደገፈኝ ምህረትህ አቆመኝ የቃልህ ፍቺ ብርሃን ሆነኝ ሞኙን ሰው አስተዋይ አደረገኝ ይኸው አለሁ እየደገፍኸኝ ተስፋ ሳትቆርጥብኝ አመሰግናለሁ ፍቅርህ ዘለዓለም ነው አመሰግናለሁ ቃል አጥሮኝ ነው /2x ሁልጊዜ አለህ ከእኔ ጋራ ከአንተ ጋር ትልቅ ሆኛለሁ በሠራኸው ሥራ