ሁሉ ወደገዛ ምቾቱ ቢሄድ ሰዉ ባይሠለፍ ለእውነት መንገድ ሆዴ ቢሞላ ባበሉኝ ሃሰት መቼም አልፈቅድ እንዲሆነኝ ሰውነት ሁሉ ወደገዛ ምቾቱ ቢሄድ ብዙም ባይገኝ እውነትን ሚወድ ሆዴ ቢሞላ ባበሉኝ ሃሰት መቼም አልፈቅድ እንዲሆነኝ ሰውነት እቆማለሁ ለእውነት እናገራለሁ ለህይወት እስከ ሞት እታገላለሁ ያለመዱኝን ሃሰት እቆማለሁ ለእውነት እናገራለሁ ለህይወት ምን ቢሰብኳት ባዶ ቢያሽሞነሙኗት ከንቱ ሲከተላት የኖረ ከመድረሻው ቀርቷል ስንቱ ይልቅ ለሞት አታዝግሙ እውነት ይጣራል ኑ ስሙ ከምድር የሚሻል አለ ከህይወት ግብዣ ታደሙ ቋሚ ውል ላልተገኘላት ለካጅ ዓለም አትሙቱ እመንገድ ቤት መቀለስ በሆድ ለሚያልፍ ከንቱ ጊዜ ስንዝር ላይሞላ ዘለዓለምን ቸል አትበሉ ምቾታችሁን ስቀሉ እውነት ይንገስ ዝቅ በሉ ሁሉ ወደገዛ ምቾቱ ቢሄድ ሰዉ ባይሠለፍ ለእውነት መንገድ ሆዴ ቢሞላ ባበሉኝ ሃሰት መቼም አልፈቅድ እንዲሆነኝ ሰውነት ሁሉ ወደገዛ ምቾቱ ቢሄድ ብዙም ባይገኝ እውነትን ሚወድ ሆዴ ቢሞላ ባበሉኝ ሃሰት መቼም አልፈቅድ እንዲሆነኝ ሰውነት እንደሚናገር መጽሃፍ ዘመኑ እንዳለ በቋፍ እውነት አይሸበር ለብዙ ባለጊዜዎች ልብ ግዙ ወደ እውነት ጓዳ ዝለቁ ለስም ትግል አትለቁ የሚረባውን አጥብቁ ለከንቱ ትርፍ አትድቀቁ እወቁ ያስገኛችሁን አትናቁ አንድ ውዳችሁን እውነት የሆነው ተወልዷል አቁሙ ፍለጋችሁን ፍቅር ሥጋ ለበሠ ሰውነት በመከራው ተፈወሠ ጨለማ በተስፋ ተገፈፈ ጽድቅ በትንሣዔው ተለፈፈ እቆማለሁ ለእውነት እናገራለሁ ለህይወት እስከ ሞት እታገላለሁ ያለመዱኝን ሃሰት እቆማለሁ ለእውነት እናገራለሁ ለህይወት