ከቀናት መሃከል በድንገት ማንም በማያውቀው ሰዓት ሁሉ እንደ ሁሌው ሲኖር ሳለ የሚሆን ልዩ ነገር አለ ይህ አብሮን የኖረ ሰማይ ከሁሉ ገዝፎ የሚታይ መከለያነቱ ይቀራል እንደ ጨርቅ ይተረተራል ዓይኖች ሁሉ ወደላይ በጉን በግርማው ልናይ በደም ተረጭቷል ልብሱ ዕዳዬን የወሠደው ንጉሡ የተጫነኝ ሃዘን መከራ የባለጋራዬ ፉከራ እንደ ጉም በኖ ሊጠፋ ከሰማይ መለከት ሲነፋ የማይዋረድ የምድር ክብር እንደፀና የሚቀር ልዕልና የለም ፍጡር የቱን ያህል ቢንጠራራ የባለቤቷ ናት ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል ዓይኖች ሁሉ ያዩታል /2x የማይዋረድ የምድር ክብር እንደፀና የሚቀር ልዕልና የለም ፍጡር የቱን ያህል ቢንጠራራ የባለቤቷ ናት ዓለም