Song Lyrics

ጥቂቱ ይበቃል

Tikitu Yibekal

በአመፅ ከተገኘ ግዝፈት የፍቅር ትንሹ ይበልጣል ከኃጥያተኛው መትረፍረፍ የፃድቁ እጦት ይበቃል ሞት ካጠላበት ከትልቁ ዋርካ የህይወት ችግኝ ብልጫ አለው ከጨለማ ከማያልቅ አምሮት ብርሀን ብቻውን አርኪ ነው የእግዚአብሔር የሆነው ጥቂቱ ይበቃል ሰው ለከንቱነት እንዲሁ ይጨነቃል የእግዚአብሔር የሆነው ጥቂቱ ይበቃል ሰው ለከንቱነት እንዲሁ ይጨነቃል ለራስ ለስጋ ከሚሸጥ ነፃነት የፍቅር ባርነት ይበጃል በግፍ በእብሪት ከዳበረን እምነት የቱትራስ መካድ ይሻላል ትርጉም ለሌለው ለውሸት ከመኖር ለእውነት መሞት ክብር ነው መጽሐፍ እንደሚል የእግዜር ሞኝነት ከሰዎች ጥበብ ጠቢብ ነው ለሞት ትርፍ ህይወት ብከፈል ምን ትርጉም አለው ስጋችን በቃኝ አያውቅም ጥበብ በመደራት ነው ጣፋጩን መብል ፍለጋ ኑሮን ከማምረር ዋናውን በልብ አንግሶ ህይወት ማሳመር የእግዚአብሔር የሆነው ጥቂቱ ይበቃል ሰው ለከንቱነት እንዲሁ ይጨነቃል የእግዚአብሔር የሆነው ጥቂቱ ይበቃል ሰው ለከንቱነት እንዲሁ ይጨነቃል ንጹን መልካሙን መውደድ መውደድ ቅዱሱን ፍፁሙን መፈለግ ከአለም ከንቱ ክምችት ክምችት ጥቂቱን በቂውን መሻት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection