Song Lyrics

አልሰማንም ወይ

አልሰማንም ወይ ጩኅት የሕፃናቱን ወዳጅ ዘመድ አጥተው ተርበው ሲያለቅሱ ጠግበን እያደርን ተርፎን ስንደፋ ምን አለ ብንሰጥ ጥቂት እንኳን ጉርሻ *2 ዝናብና ውርጩ ሲፈራረቅባቸው ሞቆን እያደርን መቼ አሰብናቸው መስጠትን ካቃተን ለኛ ከተረፈን ቅዱስ*3 አምላካችን እንዳይታዘበን/*2/ ስጋና ደማቸው ከኛ ሆኖ ሳለ በአፈር ላይ አፈር ስለምን ጨከነ ታድያ ለምን ዝም አልን ሲራቡ ሲታረዙ ሚሆኑትን አጥተው ጎዳና ሲያድሩ *2 የበረከት አምላክ መባረክን ባርከን *4 ለተገፉት መጠጊያ ማረፊያ አድርገን ለሌሎች የሚያዝን ሚራራ ልብ ስጠን*2
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection