Song Lyrics

.መንፈስ ቅዱስ

ከእስትንፋሴ ይልቅ ቅርቤ የሆንከው ማንነትህን ቃላት ገልጾ የማይጨርሰው*2 ህልውናህ ለእኔ ሁሉን ያስረሳል አንተን ማግኘቱ ብቻ እርካታን ይሰጣል *2 ሁሉን ትቼ አንተን የምናፍቀው ዘውትር የምሻው የአንተን መገኘት ነው መኖርህ አንድ ልዩ ነገር ይዟል ደስታና ሰላም እንደወንዝ ይፈሳል*2 መንፈስ ቅዱስ እፈልግሃለሁ /4*/ መገኘትህ በሚሰጠው ውበትና ግርማ ልቤ በደስታ በሚያርስ ጠል ተሞላ *2 ናፍቆቴ ይሁን ለእኔ ጌታ መገኘትህ ፍፁም ሰላሜ ያኔ ነው በአብሮነትህ *2 በማንም በምንም ማላወዳድረው የሕይወት እርካታ ማገኘው ባንተ ነው በልቤ ላይ ይፍሰስ በቤቴ ላይ ይሙላ ከቶ አይጉደልብኝ የአንተ ህልውና *2 መንፈስ ቅዱስ እፈልግሃለሁ /4*/
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection