Song Lyrics

ስላንተ

ማለዳ ብዘምር በቀትር ብዘምር ሲመሽም ብዘምር አይታክተኝም ምንም ስላንተ ማውራት እግዚአብሔር እኔ አይሰለቸኝም*2 ከመሬት ያነሰ ዝቅታ ቢኖር ከዚያም ዝቅ ብዬ ከእግርህ ስር ብሆን ያም አይበቃኝም የልቤን አይደርስም የሚገልጽህን ቃል አምላኬ አላገኝም *2 ጠዋት ትዝ ይለኛል ማታም አስባለሁ ዘወትር በመንገዴ አሰላስላለሁ ጌታ ሆይ ፍቅርህ ምንኛ ድንቅ ነው ማርኮ አስቀርቶኛል ምርኮኛ ሆኛለሁ *2 ማለዳ ብዘምር ስላንተ ምህረት ስጀምር ላወራ ቃላት ያጥረኝና ይቀድመኛል እምባ እንዴትስ ልናገር በምንስ ቋንቋ አልቻልኩም ጌታ ሆይ እንዲህ ነህ ልል እንኳ*2 ማለዳ ብዘምር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection