ክብር ለበጉ ለታረደልን ከኃጢአት ባርነት ነጻ ላወጣን የዕዳውን ጽሕፈት ለደመሰሰው ለአዳኛችን ክብር ይድረሰው *2 ስለ በደላችን ቆሰለ ሕመማችንን ታመመ ለኃጢአታችን መድኃኒት ሆነ በእርሱ ቁስል እኛን ፈወሰ/*2/ ክብር ተቅበዝብዘን ሳለ እንደሌለው ተስፋ በየመንገዳችን በዓለም እንዳንጠፋ በምህረቱ ብዛት ቤቱ አስገባን ቤዛችን ሆኖልን ልጆቹ አደረገን የማይጠፋ ሕይወት መዳን አግኝተናል በፍጹም ፍቅሩ ልጆቹ ሆነናል ሞትን አሸንፎ ሕያው አደረገን የዘለዓለምን ቤት በሰማይ ሠራልን ክብር*3 በደሙ ቤዛ ለሆነን ክብር*3 የመንግስቱ ካህናት ላረገን