እንደ እግዚአብሔር ያለ አለ ወይ*2 አይታችኋል እስቲ በምድር በሰማይ የለም የለም የለም አይኖርም ዘለዓለም*2 መለወጥ ሳያውቅ ዛሬም እንደ ጥንቱ ጸንቶ የሚኖር በብርታቱ የዘመናት ብዛት እርሱን ያላስረጀው ዘላለም የሚኖር እግዚአብሔር ነው*2 እንደ እግዚአብሔር ያለ እንደ ሳር ይደርቃል ሥጋ ለባሽ ሁሉ ነገሥታት አለቆች እንደ ወንዝ ያልፋሉ ማያልፍ የመሰለው ታሪክ ሲሆን ቀሪ ከእርሱ በቀር የለም ብቻውን ነዋሪ /*2/ ለሚታመኑበት ጋሻ፣ ከክፋት ሁሉ መሸሻ ታማኝ ነው ለሚጠብቁት በቃሉ እውነት ለቆሙት ነፍሳችንን ከሞት ወጥመድ የሚያድናት፤ ቸር እረኛ የሚራራ መልካም አባት በጥላው ሥር ያለፍርሃት እንኖራለን፤ የማይተወን የዘላለም አምላክ አለን *2 እንደ እግዚአብሔር ያለ