ና ወደ አዳኝ ና ወደ ጌታ በነጻ ተቀበል የሕይወት ስጦታ ና ወደ አዳኝ ና ወደ ጌታ ኢየሱስ ይሆንሃል ለጥምህ እርካታ *2 ከገሃነም እሳት እጅግ ከሚያስፈራ ከጨለማው መንደር ከመቃብር ስፍራ ከዓለም ከንቱነት ከሰይጣን ሽንገላ አምልጥ ወደ ሕይወት አትሁን ተላላ ና ወደ አዳኝ ዓላማ ቢስ ኑሮ የሌለው መድረሻ ያንከራትትሃል እስከመጨረሻ እውነት እና ሕይወት የፅድቅ ጎዳና ሰማይ ያደርስሃል ወደ ኢየሱስ ና ና ወደ አዳኝ በሩ ሳይዘጋ ማምለጥ አለው ዋጋ ነፍስህን አድናት በክርስቶስ ጸጋ ጉልበትህ ሳይደክም በጉብዝናህ ወራት አምልጥ እንላለን ወደ ጌታ ምህረት *2 ባለህ አትመካ ጥለህ በምትሄደው ዕውቀት ገንዘብ ዝና እዚሁ ቀሪ ነው ዛሬ ነገ አትበል ከቁጣው ፍርድ አምልጥ ከጊዜያዊው ደስታ ዘላቂውን ምረጥ *2 ና ወደ አዳኝ