ተፈርተህ የምትኖር በዙፋንህ ማንም የማይመስልህ እግዚአብሔር/*2/ ዕልፍ አዕላፍ መላዕክት የሚያመልኩህ ቅዱስ ቅዱስ እያሉህ የሚሰግዱልህ የምትመለክ አሃ ሃ ሃ የምትደነቅ የምትሞገስ/*2/ የተፈራህ ነህ ስምህ የገነነ ከሁሉም በላይ ከፍ ብለህ ያለህ በብዙ ምስጋና በክብር አጊጠህ ትኖራለህ አንተ አምረህና ደምቀህ*2 ተፈርተህ የአሕዛብ አማልክት ጣኦታት ናቸው አይሰሙም አያዩም ምንም ኃይል የላቸው የአሕዛብ አማልክት ጣኦታት ናቸው አይሄዱም አይሰሩም ምንም ኃይል የላቸው እግዚአብሔር ሰማያትን ሰራ እግዚአብሔር ምድርን አፀና *4 ትውልድ ለትውልድ ስላንተ ያወራሉ እግዚአብሔር ትልቅ ነው ግሩም ነው እያሉህ/*4/ ያመለኩሃል ያደንቁሃል ቅዱሳን በሙሉ ይዘምሩልሃል /*2/ እግዚአብሔር ሰማያትን ሰራ እግዚአብሔር ምድርን አፀና *4