Song Lyrics

የነፍሴ ፍለጋ

ጌታ ሆይ ወዴት ነህ እያልኩኝ ስምህን ስጣራ በእንብርክክ ሆኜ ላገኝህ በፀሎቴ ስፍራ ፊትህን ናፍቄ ቤቴ እንድትገባ በሬን ስታንኳኳ ቆመህ ከደጃፌ እከፍትልሃለው ድካሜን አልፌ*2 መኖር ትርጉም አለው ስሆን ካንተ ጋራ መሻቴ አንተ ነህ የሕይወት ቃል አለህና እንድትባርከኝ ልቤን እንድትነካ እፈልግሃለው አልሆንም እንደረካ *2 ናፍቆቴ ይሄ ነው መሻቴ ይሄ ነው ፍላጎቴ ይሄ ነው ክብርህን ማየት ነው /ፊትህን ማየት ነው/ አያስቀረኝ የዓለም ስበት እጠጋሃለው ዕለት ዕለት አንተን እስካይ አይዛል ጉልበቴ የነፍሴ ፍለጋ ነህና ጥማቴ *2 ናፍቆቴ ይሄ ነው ጉጉቴ ይሄ ነው ፍላጎቴ ይሄ ነው ክብርህን ማየት ነው /ፊትህን ማየት ነው/
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection