Song Lyrics

ፍቅር ነህ

በጌቴሴማኒ የደም ላብ ሲያልብህ ይታያል ጭንቀትህ እስከሞት ኀዘንህ ያንን ጣር ችለኸው ነፍስህን መስጠትህ በጭንቅ ልትወልደኝ ነው ለአዲስ ሕይወት/2/ ፍቅር(3x) ፍቅር ነህ ፍቅር ፍቅር(3x) ኢየሱስ ነህ ፍቅር ሆነኸኛል የመዳኔ ምስጢር ለዘላለም ይገባሃል ክብር(2) ኃጢአተኛ ነበርኩ ፍጹም በደለኛ ኢየሱስ ግን ጻድቅ የነፍሴ እረኛ በሞትህ ሕይወቴን አድነሃልና መስዋእቴን ላቅርብ ይብዛልህ ምስጋና *2 ፍቅር ግንበኞች የናቁት የማዕዘን ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ቤተ-መቅደስ በስጋህ ቀርቤ ወገንህ ሆኛለው ነውሬን አስወግደህ ቅዱስ ተብያለሁ*2 የለብኝም ኩነኔ ስለሞተልኝ ለኔ ሕይወትን አግኝቻለው በስሙ በማመኔ*4
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection