Song Lyrics

ተመለክ

የደመቀ ብርሃን ለብሰህ እንደሸማ እግዚአብሔር ኃያል ታላቅ ባለግርማ አምላካችን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ለታላቅነትህ መላዕክት ይሰግዳሉ እኔም ከእነርሱ ጋር አብሬ ገና አልጠገብኩም ዘምሬ ሳመልክህ ነው ደስ የሚለኝ ሳደንቅህ ነው ደስ የሚለኝ ሳላመልክህ እንዴት እውላለሁ ሳላደንቅህ እንዴት ብዬ አድራለሁ ሳመልክህ ነው እኔ ደስ የሚለኝ ሳደንቅህ ነው እኔ ደስ የሚለኝ አንተ የምትመለክ ነህ አንተ የምትደነቅ ነህ*2 የወንዝ የፏፏቴው የተራሮች ግርማ ሥራህን ያውጃሉ በሚጣፍጥ ዜማ ፍጥረታት ሲያከብሩህ ቃላቸው ተሰማ እኔም ከእነርሱ ጋር አብሬ ገና አልጠገብኩም ዘምሬ ሳመልክህነው ደስ የሚለኝ ሳደንቅህ ነው ደስ የሚለኝ *2 ተመለክ በዙፋንህ ላይ በላይ በሰማይ ተመለክ ባለህበት በማደሪያህ ላይ ተመለክ የልቤ አምላኬ ሆይ ለዘለዓለም ተመለክ እወድሀለሁኝ ዛሬም ቢሆን ነገም ሳላመልክህ አመልክሃለው *4
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection