ለባዘነች ነፍሱ እረፍትን ፍለጋ በምድራዊ ነገር በሚያልፍ የተመካ ሰው እንኳን ሰው ታምኖ እኔ አልሰጋም ይላል እኔ አንተን ታምኜ እንዴት አልመካም እህ እህህ ሰው አይደለህማ እህ እህህ አትተወኝማ *2 በሥጋ ለባሽ ላይ ልብ እንዴት ይጣላል እንደ ሸንበቆ ነው ድንገት ይሰበራል*2 የጸና ግንብ ነህ ባንተ እታመናለው ማትሰበር ምርኩዝ እደገፍሃለው *2 ሰው እንኳን የተናገርከው ቃል ያልከው ሆኖልኛል ታማኝነትህን ታሪክ ይናገራል ለነገውም ቢሆን ለምን እሰጋለሁ ሐሳቤን በሙሉ ባንተ ላይ ጥያለሁ/*5/ አንተ አትቀየርም ስለዚህ ተስፋዬን አልቆርጥም አንተ አትለወጥም ስለዚህ ተስፋዬን አልቆርጥም አይደለም በሚታይ በሚዳሰሰው/2 የእኔ መታመኛ እግዚአብሔር ነው።*2