Song Lyrics

ይወጣል

Hirut Moges
Lateterahulet Alinorim
ከእግዚኣብሔር ጋር የሆነውን ሰው ማን ይረታል? ኦሆሆ ማን ይረታል? ኦሆሆ ማን ይረታል? ኦሆሆ በድል ወጥቶ በድል ይገባል ያሸንፋል ኦሆሆ ያሸንፋል ኦሆሆ ያሸንፋል ኦሆሆ ጌታ ከእርሱ ጋር የሆነ ሰው ኦሆሆ ይወጣል ይወርሳል ያስወርሳል (4x) ኦሆሆ ሁለቱ ብቻ ተለይተው ከአሥሩ የዕምነት ቃል በድፍረት ሲናገሩ መውረስ ብቻ ነበር የሚታያቸው እንውጣና እንውረስ ነው ቋንቋቸው እንዲሁ እንዳሉት ሆነላቸው እግዚኣብሔርም ተስፋቸውን አስወረሳቸው እንደ ካሌብ ኦሆሆ እንደ ኢያሱ እኔንም አርገኝ ጌታዬ እንደነርሱ የእግዚኣብሔር ሰው ሽንፈትን አያወራም በሚሰማው በሚታየው አይፈራም የፊቱን ሊይዝ የኃላውን ይረሳል ቃል ስላለው የረገጠውን ይወርሳል እርሱማ ከሰው ሁሉ ይለያል እግዚኣብሔር ያየውን ብቻ ያያል ፊት ለፊት ገጥሞ ኦሆሆ ከጠላቱ ባለድል እርሱ ይሆናል በጦርነቱ የእግዚኣብሔር ሰው ሲናገር ያስተውላል መልካም ነገር አድሮ ሲያስብ አድሮ ይውላል ዋዘኞችን ፌዘኞችን ይጠላል ለያዘው ዕውነት እስከ ሞት ይጨክናል እሱማ ነው የአስተዋይ ባልንጀራ ዕውነት ብቻ በአፍ የሚያወራ ለራዕዩ ዋጋ ይከፍላል ይለፋል በዘመኑም ቁምነገር ሠርቶ ያልፋል ምሣሌ ሆኖ ኦሆሆ ለሰው ሁሉ በድል ይወጣል ይገባል ታምኖ በቃሉ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection