አምላኬን ከልብ ኦሆሆ አመልካለሁ ልዘምርለት ኦሆሆ ተለይቻለሁ አከብረዋለሁ ኦሆሆ ዛሬም በደስታ ሥራዬ ሆኖአል ኦሆሆ መኖር ለጌታ ያዘምረኛል ቅባቱ ያዘምረኛል ያዘምረኛል ምሕረቱ ያዘምረኛል ያዘምረኛል እሳቱ ያዘምረኛል እኔን ጌታ እኔን ኢየሱስ አመልክህ ዘንድ ጠርተኸኛል አከብርህ ዘንድ መርጠኸኛል አመልክህ ዘንድ ጠርተኸኛል እኔም አንተ ኦሆሆ መድሃኒቴን አሀሀ መመኪያዬ ኦሆሆ ማለፊያዬም አሀሀ በሙሉ ሃይሌ ኦሆሆ በአዳዲስ ዕቅዴ አሃሃ አመልክሃለሁ ኦሆሆ አከብርሃለሁ ኦሆሆ ሥራዬ እኮ ነው በቃ (4x) እኔማ ለሃሜት ጊዜ የለኝም በማንም ለመፍረድ ጌታ አልጠራኝም የታዘዝኩትን ቁምነገር ልሰራ ጊዜ አልበቃኝም እኔ ፅድቅን አላወራም ለተንኮል ለአመጽ ለክፋት አዝ፦ አልተጠራሁም ለወሬ አልተጠራሁም ለሃሜት አልተጠራሁም ለትችት አልተጠራሁም ላልተጠራሁለት እኔ አልኖርም የጠራኝን ጌታ አላሳፍርም ታማኝ አርጎ ቆጥሮ በቤቱ ሲሾመኝ ጌታዬ ለራሱ ለይቶ ሲያቆመኝ እኔስ ለምን ልሂድ ወደ ውርደት ስፍራ ወደተውኳት አለም ሃጥያት ልሰራ አዝ፦ አልተጠራሁም ለአለም አልተጠራሁም ለሃጥያት ለውሽት ለስርቆት ለዝሙት አልተጠራሁም ለርኩሰት አልተጠራሁም ላልተጠራሁለት አልኖርም የጠራኝን ጌታ አላሳፍርም ማን እንደሆንኩኝ እኔ እራሴን አውቃለሁ እግዚኣብሔር ሲያከብረኝ እንዴት እቀላለሁ ለትልቅ አላማ ጌታ እኔን መርጦኛል ደግሞም ለሰማዩም መንግስት አጭቶኛል አዝ፦ አልተጠራሁም ለጥፋት አልተጠራሁም ለመቅሰፍት ለሽንፈት ለውርደት ለውድቀት አልተጠራሁም ለርግማን አልተጠራሁም ላልተጠራሁለት እኔ አልኖርም የጠራኝን ጌታ አላሳፍርም